21 በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል።
22 በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።
23 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር።
24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቊጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቊጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።
25 የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።
26 የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።
27 ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።