25 የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።
26 የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።
27 ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።
28 ጌድራዊው በአልሐናን በምራባዊው ኰረብታዎች ግርጌ ለሚግኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ።
29 ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።
30 እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ።ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።
31 አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።