30 እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ።ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።
31 አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።
32 አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
33 አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።
34 የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ።ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።