16 የኢዮአቄም ዘሮች፤ልጁ ኢኮንያ፣ልጁ ሴዴቅያስ።
17 የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ልጁ ሰላትያል፣
18 መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።
19 የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ።የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤ሜሱላም፣ ሐናንያ፤እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።
20 ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።
21 የሐናንያ ዘሮች፤ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።
22 የሴኬንያ ዘሮች፤ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ ባጠቃላይ ስድስት ነበሩ።