4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤
5 በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።
6 እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
7 ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣
8 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።
9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
10 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤የሮብዓም ልጅ አቢያ፣የአቢያ ልጅ አሳ፣የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣