1 የይሁዳ ዘሮች፤ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።
2 የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው።
3 የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።
4 ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።
5 የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።