10 ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፤ ከሥቃይና ከጒዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
11 የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ።
12 ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒር ናሐሽን ከተሞች የቈረቈረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
13 የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ጎቶንያል፣ ሠራያ።የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ሐታት፣ መዖኖታይ።
14 መዖኖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ።ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።
15 የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም።የኤላ ልጅ፤ቄኔዝ።
16 የይሃሌልኤል ወንዶች ልጆች፤ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣ አሣርኤል።