3 የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።
4 ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።
5 የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።
6 ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።
7 የሔላ ወንዶች ልጆች፤ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።
8 የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።
9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።