1 ዜና መዋዕል 4:35-41 NASV

35 ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ ልጅ፣ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ

36 እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆባ፣ የሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓዲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣

37 የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፤

38 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤

39 እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተ ምሥራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።

40 በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው።

41 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።