1 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።
2 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
3 የእምበረም ልጆች፤አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም።የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣ አብዮድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።
4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤
5 አቢሱ ቡቂን ወለደ፤ቡቂ ኦዚን ወለደ፤