22 የቀዓት ዘሮች፤ልጁ አሚናዳብ፣ ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣
23 ልጁ ሕልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ ልጁ አሴር፣
24 ልጁ ኢኢት፣ ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል።
25 የሕልቃና ዘሮች፤አማሢ፣ አኪሞት።
26 ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣
27 ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።
28 የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።