68 ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣
69 ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።
70 እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።
71 ጌድሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
72 ከይሳኮርም ነገድ፣ቃዴስን፣ ዳብራትን
73 ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
74 ከአሴር ነገድመዓሳልን፣ ዓብዶን፣