73 ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
74 ከአሴር ነገድመዓሳልን፣ ዓብዶን፣
75 ሑቆቅንና፣ ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
76 ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
77 ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጐሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ወሰዱ፤ከዛብሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን፣ ሬሞንና፣ ታቦርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
78 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ኪኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሳን፣
79 ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤