5 ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6 በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7 ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8 ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣
10 ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
11 ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።