35 የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
36 የበኵር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣
37 ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩር፣ ሚቅሎት ነበሩ።
38 ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
39 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።
40 የዮናታን ወንድ ልጅ፤መሪበኣል ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።
41 የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።