38 ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
39 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።
40 የዮናታን ወንድ ልጅ፤መሪበኣል ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።
41 የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።
42 አካዝ የዕራን ወለደ፤ የዕራም ናሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
43 ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁ ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፣ ልጁ ኤሴል።
44 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።