2 እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
3 በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ።
4 ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣እርሱንም በቤቴል አገኘው፤በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤
5 እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር፣የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው።
6 ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ዘወትርም በአምላክህ ታመን።
7 ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤ማጭበርበርንም ይወዳል።
8 ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤“እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”