1 ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም።
2 አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤ሁሉም የባለ እጅ ሥራ ናቸው።ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሎአል፤“ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ”
3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣ከዐውድማ እንደሚጠረግ ዕብቅ፣በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።
4 “እኔ ግን ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።
5 በምድረ በዳ፣በሐሩር ምድርም ተንከባከብሁህ።
6 ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ከዚያም ረሱኝ።