2 ስለዚህ በዐሥራ አምስት ሰቅል ጥሬ ብርና በአንድ ቆሮስ ተኩል መስፈሪያ ገብስ ገዛኋት።
3 እኔም፣ “ከእኔ ጋር ብዙ ቀን ተቀመጪ፤ አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት።
4 እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፣ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዐምደ ጣዖት፣ ያለ ኤፉድና ያለ ጣዖት ምስል ይኖራሉና።
5 ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።