3 “ንጉሡን በክፋታቸው፣አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።
4 ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣እንደሚነድ ምድጃ፣ሁሉም አመንዝራ ናቸው።
5 በንጉሣችን የበዓል ቀን፣አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።
6 ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤በተንኰል ይቀርቡታል፤ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤እንደሚነድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።
7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዦቻቸውን ፈጁ፤ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።
8 “ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9 እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤እርሱ ግን አላስተዋለም።ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤እርሱ ግን ልብ አላለም።