9 ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ወደ አሦር ሄደዋልና፤ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።
10 በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤በኀያል ንጉሥ ጭቈና ሥር፣እየመነመኑ ይሄዳሉ።
11 “ኤፍሬም ለኀጢአት ማስተስረያ ብዙ መሠዊያዎችን ቢሠራም፣እነርሱ የኀጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆነውበታል።
12 በሕጌ ውስጥ ያለውን ብዙውን ነገር ጻፍሁላቸው፤እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት።
13 ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ወደ ግብፅም ይመለሳሉ።
14 እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ቤተ መንግሥቶችንም ሠራ፤ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አበዛ፤እኔ ግን በከተሞቻቸው ላይ እሳትን እለቃለሁ፤ምሽጎቻቸውንም ይበላል።”