ሆሴዕ 9:3-9 NASV

3 በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።

4 የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈሱም፤መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ።ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።

5 በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?

6 ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች።የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ድንኳኖቻቸውም እሾኽ ይወርሰዋል።

7 የቅጣት ቀን መጥቶአል፤የፍርድም ቀን ቀርቦአል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ!ኀጢአታችሁ ብዙ፣ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ነቢዩ እንደ ሞኝ፣መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሮአል።

8 ነቢዩ ከአምላኬ ጋር ሆኖ፣የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ዳሩ ግን በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ፣በአምላኩም ቤት ጠላትነት ይጠብቀዋል።

9 በጊብዓ እንደ ነበረው፣በርኵሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።