4 በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤በሐዘን እንጒርጒሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤የወገኔ ርስት ተከፋፍሎአል።ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’
5 ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።
6 ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።
7 የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን?“የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን?እንዲህ ያሉት ነገሮችንስ ያደርጋልን?”“መንገዱ ቀና ለሆነ፣ቃሌ መልካም አያደርግምን?
8 በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ ጠላት ሆናችሁተነሣችሁ፤የጦርነት ሐሳብ ሳይኖራቸው፣በሰላም ከሚያልፉ ሰዎች ላይ፣ማለፊያ መጐናጸፊያ ገፈፋችሁ።
9 ከሚወዱት ቤታቸው፣የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው፣ለዘላለም ወሰዳችሁ።
10 ተነሡና፤ ከዚያ ሂዱ፤ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ምክንያቱም ረክሶአል፤ክፉኛም ተበላሽቶአል።