13 ተክልሽ ሮማን፣ምርጥ ፍሬዎች፣ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው።
14 እንዲሁም ናርዶስና ቀጋ፣ጠጅ ሣርና ቀረፋ፣የተለያዩ የዕጣን ዛፎች፣ከርቤና እሬት፣ምርጥ ቅመሞች ሁሉ አሉበት።
15 አንቺ የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣ከሊባኖስ የሚወርድ፣የፈሳሽ ውሃ ጒድጓድ ነሽ።
16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና!መዐዛው ያውድ ዘንድ፣በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።