3 ሁለት ጡቶችሽ፣መንታ የዋልያ ግልገሎችን ይመስላሉ።
4 ዐንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ መጠበቂያ ማማ ነው፤ዐይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ እንዳሉት፣እንደ ሐሴቦን ኵሬዎች ናቸው፤አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከት፣እንደ ሊባኖስ መጠበቂያ ማማ ነው።
5 የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ጠጒርሽ የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው፤ንጉሡም በሹሩባሽ ታስሮ ተይዞአል።
6 እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ የምትይ ነሽ!ፍቅሬ ሆይ፤ የምታስደስቺ ነሽ።
7 ቁመናሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ መለል ያለ ነው፤ጡቶችሽም የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ።
8 እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ።ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኰይ ፍሬ ይሁኑ፤
9 ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ።የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።