7 ቁመናሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ መለል ያለ ነው፤ጡቶችሽም የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ።
8 እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ።ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኰይ ፍሬ ይሁኑ፤
9 ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ።የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።
10 እኔ የውዴ ነኝ፤የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ።
11 ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤
12 ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣አበባው ፈክቶ፣ሮማኑ አፍርቶ እንደሆነ እንይ፤በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።