2 እርሱም እንዲህ አለ፤“እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጒዳል፤የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጎአል።”
3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣ ገለዓድንአሂዳለችና፤
4 የወልደ አዴርን ምሽጎች እንዲበላ፣ በአዛሄልቤት ላይ እሳት እሰዳለሁ።
5 የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣በአዌን ሸለቆ ያለውን ንጉሥ እደመስሳለሁ፤የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል”ይላል እግዚአብሔር።
6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ለኤዶም ሸጣለችና።
7 ምሽጎቿን እንዲበላ፣በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።
8 በአስቀሎና በትር የያዘውን፣የአሸዶድንም ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰውእስኪሞት ድረስ፣እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።