አሞጽ
ምዕራፎች 2
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና፤
2የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መሐል፣በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።
3ገዧን እደመስሳለሁ፣አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር እገድላለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።
4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።
5የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ።