12 “እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።
13 “እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅ፣እኔም አደቃችኋለሁ።
14 ፈጣኑ አያመልጥም፤ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።
15 ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።
16 ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣በዚያ ቀን ዕራቁታቸውን ይሸሻሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።