13 “እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅ፣እኔም አደቃችኋለሁ።
14 ፈጣኑ አያመልጥም፤ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።
15 ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።
16 ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣በዚያ ቀን ዕራቁታቸውን ይሸሻሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።