4 አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣በጫካ ውስጥ ይጮኻልን?ምንም ነገርስ ሳይዝ፣በዋሻው ውስጥ ያገሣልን?
5 ወጥመድ ሳይዘረጋ፣ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን?የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን?
6 የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ሰዎች አይደነግጡምን?ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩንለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ምንም ነገር አያደርግም።
8 አንበሳ አገሣ፤የማይፈራ ማን ነው?ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ትንቢት የማይናገር ማን ነው?
9 ለአዛጦን ምሽግ፣ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤“በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”
10 “ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤”ይላል እግዚአብሔር።