አሞጽ 4:3-9 NASV

3 እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

4 “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5 እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋናመሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6 በየከተማው ሆዳችሁን ባዶ አደረግሁት፤በየመንደሩም የምትበሉትንአሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

7 “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ዝናብ ከለከልኋችሁ፤በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብአደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

8 ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።

9 “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”ይላል እግዚአብሔር።