1 የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤
2 “ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ከእንግዲህም አትነሣም፤በገዛ ምድሯ ተጣለች፤የሚያነሣትም የለም።”
3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ ሺህ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”
4 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”