አሞጽ 5:12-18 NASV

12 ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ፣በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና።ጻድቁን ትጨቊናላችሁ፤ጒቦም ትቀበላላችሁ፤በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።

13 ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።

14 በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፣መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራችሁት፣የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።

15 ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ፤ምናልባትም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል።

16 ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤ ገበሬዎች ለልቅሶ፣አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ።

17 በየወይኑ ዕርሻ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤እኔ በመካከላችሁ አልፋለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።

18 የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ፣ለእናንተ ወዮላችሁ የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትሻላችሁ?ያ ቀን ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።