1 በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!
2 ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጌትም ውረዱ፤እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታቶቻችሁ ይሻላሉን?የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን?
3 ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!
4 በዝሆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤
5 ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣
6 በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!
7 ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።