7 ይህንም ደግሞ አሳየኝ፤ ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር አጠገብ ቆሞ ነበር።
8 እግዚአብሔር፣ “አሞጽ፣ የምታየው ምንድ ነው?” አለኝ።እኔም፣ “ቱምቢ” አልሁ።ጌታም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።
9 “የይስሐቅ ማምለኪያ ኮረብታዎች ባድማ ይሆናሉ፤የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።”
10 ከዚህ በኋላ የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፤
11 አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበርና፤“ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፤እስራኤልም በእርግጥ ከትውልድ አገሩተማርኮ ይሄዳል።”
12 አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለ ራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።
13 ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ የንጉሡ መቅደስ፣ የመንግሥቱም መኖሪያ ነውና።”