1 ንጉሥ ጠረክሲስ እስከ ባሕር ዳርቻ በሚዘልቀው ግዛቱ ሁሉ ላይ ግብር ጣለ።
2 የኀይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ እንዲሁም ንጉሡ መርዶክዮስን ለዚህ የላቀ ማዕረግ እንዴት እንዳደረሰው የሚናገረው በሜዶንና በፋርስ የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
3 አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕረግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።