Bible
Now
Toggle navigation
ምዕራፎች
9
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽
Enable dark mode
ምዕራፎች
9
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽ Dark mode
›
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
›
ብሉይ ኪዳን
›
አስቴር
›
አስቴር 9
አስቴር
ምዕራፎች 9
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አስቴር 8
አስቴር 10
የአይሁድ ድል ማድረግ
1
አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን፣ በንጉሡ ትእዛዝ የወጣው ዐዋጅ የሚፈጸምበት ዕለት ነበር። በዚህም ዕለት የአይሁድ ጠላቶች የበላይነቱን እንደሚያገኙ ተማምነው ነበር፤ ሁኔታው ግን ተለወጠና አይሁድ በሚጠሏቸው ላይ የበላይነትን አገኙ።
2
የእነርሱን መጥፋት በሚፈልጉ ወገኖች ላይ አደጋ ለመጣል አይሁድ በንጉሥ ጠረክሲስ አውራጃዎች ሁሉ ባሉት ከተሞቻቸው ተሰበሰቡ። የሌሎቹ አገር ዜጎች ሕዝብ ሁሉ ፈርተዋቸው ስለ ነበር፣ ማንም ሊደፍራቸው አልቻለም።
3
የየአውራጃው መኳንንት ሁሉ፣ እንደራሴዎች፣ የአውራጃ ገዦች እንዲሁም የንጉሡ አስተዳዳሪዎች አይሁድን ረዷቸው፤ ይህን ያደረጉትም መርዶክዮስን ስለ ፈሩ ነበር።
4
መርዶክዮስ በቤተ መንግሥቱ ታዋቂ ሆነ፤ ዝናው በየአውራጃው ሁሉ ተሰማ፤ ኀይሉም እየበረታ ሄደ።
5
ስለዚህ አይሁድ ጠላቶቻቸውን ሁሉ በሰይፍ እየመቱ ገደሏቸው፤ አጠፏቸውም፤ በሚጠሏቸውም ላይ ደስ ያላቸውን አደረጉ።
6
አይሁድ በሱሳ ግንብ አምስት መቶ ሰው ገደሉ፤ አጠፉም።
7
ፖርሻንዳታን፣ ደልፎንን፣ አስፓታን፣
8
ፖራታን፣ አዳልያን፣ አሪዳታን፣
9
ፓርማ ሽታን፣ አሪሳይን፣ አሪዳይንና ዋይዛታንም ገደሉ፤
10
እነዚህም የአይሁድ ጠላት የሆነው የሐመዳቱ ልጅ የሐማ ዐሥር ወንዶች ልጆች ነበሩ። በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።
11
በሱሳ ግንብ የተገደሉት ሰዎች ብዛት በዚያኑ ዕለት ለንጉሡ ተነገረው።
12
ንጉሡም ንግሥት አስቴርን፣ “አይሁድ በሱሳ ግንብ አምስት መቶ ሰውና ዐሥሩን የሐማ ልጆች ገድለዋል፤ አጥፍተዋልም። በተቀሩት በንጉሡ አውራጃዎችስ ምን አድርገው ይሆን? አሁንስ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? ይፈቀድልሻል” አላት።
13
አስቴርም፣ “ንጉሥን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፣ በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ የዛሬውን ዐዋጅ ነገም እንዲደግሙት ፈቃድህ ይሁን፤ዐሥሩ የሐማ ወንዶች ልጆችም ዕንጨት ላይ ይሰቀሉ” አለች።
14
ንጉሡም ይህ እንዲሆን አዘዘ። በሱሳ ዐዋጅ ተነገረ፤ ዐሥሩንም የሐማ ወንዶች ልጆች ሰቀሏቸው።
15
በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ አዳር በተባለው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በአንድነት መጡ፤ በሱሳም ሦስት መቶ ሰዎች ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።
16
በዚህ ጊዜ በሌሎች በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩ የተቀሩት አይሁድ ራሳቸውን ለመከላከልና ከጠላቶቻቸውም ለመገላገል ተሰበሰቡ፤ ከሚጠሏቸውም ሰባ አምስት ሺህ ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።
17
ይህ የሆነው አዳር በተባለው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን ነበር፤ በዐሥራ አራተኛው ቀን ዐረፉ፤ ዕለቱንም የተድላና የደስታ ቀን አድርገው ዋሉ።
የፉሪም በዓል መከበር
18
በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ ግን በዐሥራ ሦስተኛውና በዐሥራ አራተኛው ቀን ተሰብስበው ነበር፤ ከዚያም በዐሥራ አምስተኛው ቀን ዐረፉ፤ ዕለቱንም የተድላና የደስታ ቀን አድርገው ዋሉ።
19
በየመንደሩ የሚኖሩ የገጠር አይሁድ፣ የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን የተድላና የደስታ፣ እርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚለዋወጡበት ቀን አድርገው የሚያከብሩት ከዚሁ የተነሣ ነው።
20
መርዶክዮስ የተፈጸሙትን እነዚህን ድርጊቶች ጻፈ፤ ደብዳቤ አዘጋጅቶም በመላው የንጉሥ ጠረክሲስ አውራጃ በቅርብና በሩቅ ለሚገኙት አይሁድ ሁሉ ላከ፤
21
የላከውም የአዳርን ወር ዐሥራ አራተኛና ዐሥራ አምስተኛ ቀን በየዐመቱ እንዲያከብሩ ነው፤
22
የሚያከብሩበትም ምክንያት አይሁድ ከጠላቶቻቸው ዕረፍት ያገኙበት፣ ሐዘናቸው ወደ ደስታ፣ ልቅሷቸውም ወደ ክብረ በዓል የተለወጠበት ቀን ስለ ሆነ ነው። ቀኖቹንም የተድላና የደስታ ቀኖች አድርገው፣ እርስ በርሳቸውም የምግብ ስጦታ እየተለዋወጡና ለድኾችም ስጦታ እየሰጡ እንዲያከብሩ ጻፈላቸው።
23
ስለዚህ አይሁድ መርዶክዮስ የጻፈላቸውን ለመፈጸምና የጀመሩትን በዓል ለማክበር ተስማሙ፤
24
ምክንያቱም የአይሁድ ሁሉ ጠላት የሆነው የአጋጋዊው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ አይሁድን ለማጥፋት አሢሮ ነበር፤ ሊፈጃቸውና ሊያጠፋቸውም ፉር የተባለ ዕጣ ጥሎ ነበር።
25
ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።
26
ስለዚህ እነዚህ ቀኖች ፉር ከሚለው ቃል “ፉሪም” ለመባል በቁ። በዚህ ደብዳቤ ስለ ተጻፈው ሁሉ፣ ስላዩትና ስለ ደረሰባቸውም ነገር ሁሉ፣
27
አይሁድ በታዘዘውና በተወሰነው ጊዜ እነርሱና ዘሮቻቸው፣ እነርሱን የተጠጓቸውም ሁሉ እነዚህን ሁለት ቀኖች በየዓመቱ ባለማቋረጥ እንዲያከብሩ ሥርዐት አድርገው ራሳቸው ወሰኑ።
28
እነዚህም ቀኖች በእያንዳንዱ ትውልድ፣ በእያንዳንዱ ቤተ ሰብ፣ በእያንዳንዱ አውራጃና በእያንዳንዱ ከተማ መታሰብና መከበር ይኖርባቸዋል፤ ይኸውም እነዚህ የፉሪም ቀኖች በአይሁድ ዘንድ ሳይከበሩ እንዳይቀሩ፤ መታሰቢያቸውም ከዘሮቻቸው መካከል እንዳይደመሰስ ነው።
29
ስለዚህ የአቢካኢል ልጅ ንግሥት አስቴር ከአይሁዳዊው ከመርዶክዮስ ጋር በመሆን፣ ፉሪምን አስመልክተው ይህችን ሁለተኛዪቱን ደብዳቤ ለማጽናት በሙሉ ሥልጣን ጻፉ።
30
መርዶክዮስም የመልካም ምኞት መግለጫና ማረጋገጫ የሆነውን ደብዳቤ በጠረክሲስ ግዛት ውስጥ በሚገኙት አንድ መቶ ሃያ ሰባት አውራጃዎች ለሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ላከ፤
31
የላከውም አይሁዳዊው መርዶክዮስና ንግሥት አስቴር ባወጁላቸውና እንደዚሁም የጾሙንና የሰቈቃውን ጊዜ በሚመለከት ለራሳቸውና ለዘራቸው ባጸኑት ውሳኔ መሠረት እነዚህ የፉሪም ቀኖች በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲከበሩ ነው።
32
የአስቴር ዐዋጅ ስለ ፉሪም የወጣውን ሥርዐት አጸና፤ ይህም በመዝገብ ተጻፈ።
አስቴር 8
አስቴር 10
ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10