1 ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤መልእክተኛውም ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህብሎአል፤“ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”
2 “እነሆ፤ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፤እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።
3 አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥየምትኖር፣መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ለራስህም፣“ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?” የምትል፣የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።
4 እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ከዚያ አወርድሃለሁ”ይላል እግዚአብሔር።