4 ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፤ፍትሕ ድል አይነሣም፤ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣ክፉዎች ጻድቃንን ይከባሉ።
5 “ቢነገራችሁም እንኳ፣የማታምኑትን እናንተን፣በዘመናችሁ አንድ ነገር ስለማደርግ፣እነሆ፤ ሕዝቡን እዩ፤ ተመልከቱም፤እጅግም ተደነቁ።
6 የራሳቸው ያልሆኑትን መኖሪያ ስፍራዎች ለመያዝ፣ምድርን ሁሉ የሚወሩትን፣ጨካኝና ፈጣን የሆኑትን፣ባቢሎናውያንን አስነሣለሁ።
7 እነርሱም የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ፍርዳቸውና ክብራቸው፣ከራሳቸው ይወጣል።
8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው።ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ።ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል አሞራ ይበራሉ፤
9 ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ።ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል።
10 ነገሥታትን ይንቃል፤በገዦችም ላይ ያፌዛል፤በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤የዐፈር ቊልል ሠርቶም ይይዘዋል።