ዕንባቆም 1:7-13 NASV

7 እነርሱም የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ፍርዳቸውና ክብራቸው፣ከራሳቸው ይወጣል።

8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው።ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ።ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል አሞራ ይበራሉ፤

9 ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ።ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል።

10 ነገሥታትን ይንቃል፤በገዦችም ላይ ያፌዛል፤በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤የዐፈር ቊልል ሠርቶም ይይዘዋል።

11 ከዚያም በኋላ እንደ ነፋስ ዐልፎ ይሄዳል፤ጒልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።

12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን?የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ እኛ አንሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ዐለት ሆይ፤ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው።

13 ዐይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ እጅግ ንጹሓን ናቸው፤አንተ በደልን መታገሥ አትችልም፤ታዲያ፣ አታላዮችን ለምን ትታገሣለህ?ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣ለምን ዝም ትላለህ?