18 በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር አገልግሎት ካህናቱን በየማዕረጋቸው፣ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቧቸው።
19 ምርኮኞቹ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ።
20 ካህናቱና ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ሁሉም በሥርዐቱ መሠረት ነጽተው ነበር። ሌዋውያኑም የፋሲካውን በግ ለምርኮኞቹ ሁሉ፣ ለካህናት ወንድሞቻቸውና ለራሳቸው ዐረዱ።
21 ስለዚህ ከምርኮ የተመለሱት እስራኤላውያን የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በአምልኮ ይፈልጉት ዘንድ ራሳቸውን ከአረማውያን ጎረቤቶቻቸው ርኵሰት ከለዩት ሁሉ ጋር በሉ።
22 እግዚአብሔር ደስ እንዲሰኙ ስላደረጋቸው የቂጣን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ልብ ለውጦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤት ሥራ እንዲያግዛቸው አድርጎ ነበር።