1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከባቢሎን አብረውኝ የወጡት የየቤተ ሰቡ አለቆችና አብረዋቸው የተመዘገቡት እነዚህ ናቸው፤
2 ከፊንሐስ ዘሮች ጌርሶን፤ከኢታምር ዘሮች ዳንኤል፤ከዳዊት ዘሮች ሐጡስ፤
3 እርሱም ከሴኬንያ ዘሮች ነው፤ከፋሮስ ዘሮች ዘካርያስና ከእርሱም ጋር 150 ወንዶች ተመዝግበው ነበር፤
4 ከፋሐት ሞዓብ ዘሮች የዘራእያ ልጅ ኤሊሆ ዔናይና ከእርሱም ጋር 200 ወንዶች፤