1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤
2 “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቶአልና።”
3 ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፣ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጒዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።
4 እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች።
5 መርከበኞቹ ሁሉ ፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱም ክብደት እንዲቀል፣ በውስጧ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕሩ ጣሉት።ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ፤ በከባድም እንቅልፍ ላይ ነበር።