ዳንኤል 2:21-27 NASV

21 ጊዜንና ወቅትን ይለውጣል፤ነገሥታትን በዙፋን ያስቀምጣል፣ደግሞም ያወርዳቸዋል፤ጥበብን ለጠቢባን፣ዕውቀትንም ለሚያስተውሉ ይሰጣል።

22 የጠለቀውንና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤በጨለማ ያለውን ያውቃል፤ብርሃንም ከእርሱ ጋር ይኖራል።

23 የአባቶቼ አምላክ ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ፤አከብርሃለሁም፤ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛልና፤ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤የንጉሡን ሕልም አሳውቀኸናል።”

24 ዳንኤልም የባቢሎንን ጠቢባን እንዲገድል ንጉሡ ወዳዘዘው ወደ አርዮክ ሄዶ፣ “የባቢሎንን ጠቢባን አትግደል፤ ወደ ንጉሡ ውሰደኝ፤ እኔም ሕልሙን እተረጒምለታለሁ” አለው።

25 አርዮክም ዳንኤልን ወዲያውኑ ወደ ንጉሡ በመውሰድ፣ “ሕልሙንና ትርጒሙን ለንጉሡ መግለጥ የሚችል ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቻለሁ” አለው።

26 ንጉሡም ብልጣሶር የተባለውን ዳንኤልን፣ “ያየሁትን ሕልምና ትርጒሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?” አለው።

27 ዳንኤልም እንዲህ አለ፤ “አንድም ጠቢብ፣ አስማተኛ፣ ጠንቋይም ሆነ ቃላተኛ ንጉሡ የጠየቀውን ምስጢር መግለጥ የሚችል የለም፤