20 በሌላ ስፍራ ደግሞ፣ “ጌታ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ መሆኑን ያውቃል” ተብሎ ተጽፎአል፤
21 እንግዲህ ማንም በሰው አይመካ። ሁሉ ነገር የእናንተ ነውና፤
22 ጳውሎስም ሆነ አጵሎስ ወይም ኬፋ፣ ዓለምም ሆነ ሕይወት ወይም ሞት፣ አሁን ያለውም ሆነ ወደ ፊት የሚመጣው፣ ሁሉ የእናንተ ነው፤
23 እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።