2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ እንግዲያው፣ በትንሹ ነገር ላይ ለመፍረድ አትበቁምን?
3 በምድራዊ ሕይወት ጒዳይ ቀርቶ፣ በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን?
4 እንግዲህ እንዲህ ያለ ጒዳይ ሲያጋጥ ማችሁ፣ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጅ አድርጋችሁ ሹሟ!
5 ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ ከመካካላችሁ ወንድሞችን ለማስታረቅ የሚበቃ አስተዋይ ሰው የለምን?
6 ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ለመክሰስ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ያውም በማያምኑ ሰዎች ፊት!
7 እንግዲህ በመካከላችሁ መካሰስ መኖሩ ራሱ ውድቀታችሁን ያሳያል። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?
8 እናንተ ግን ራሳችሁ ትበድላላችሁ፤ ታታልላላችሁም፤ ያውምኮ ወንድሞቻችሁን።