2 ቆሮንቶስ 13:1-7 NASV

1 ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ መሆኑ ነው፤ “ማንኛውም ነገር በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ይጸናል።”

2 በሁለተኛው ጒብኝቴ እናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፤ አሁንም በሩቅ ሆኜ እንደ ገና አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ወደ እናንተም ተመልሼ ስመጣ ከዚህ በፊት ኀጢአት ለሠሩትም ሆነ ለሌሎች አልራራላቸውም፤

3 ይህም የሚሆነው ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው። እርሱም በመካከላችሁ ብርቱ እንጂ ደካማ አልነበረም።

4 የተሰቀለው በድካም ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ኀይል ሕያው ሆኖ ይኖራል። እኛም በእርሱ ደካሞች ብንሆንም፣ እናንተን ለማገልገል ግን በእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ሕያዋን ሆነን እንኖራለን።

5 በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በስተቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?

6 እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነ ዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

7 አሁንም ምንም ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም እኛ ብቁዎች እንደሆንን ሰዎች እንዲያዩልን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም እንኳ ብቁዎች ባንሆንም እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው።