19 በላይ በሰማያት ድንቅ ነገሮችን፣አሳያለሁ፤ በታች በምድርም ምልክቶችን እሰጣለሁ፤ደምና እሳት፣ የጢስም ጭጋግ ይሆናል።
20 ታላቅና ክቡር የሆነው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ፀሓይ ወደ ጨለማ፣ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።
21 የጌታን ስም፣የሚጠራ ሁሉ ይድናል።’
22 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ይህን ቃል ስሙ፤ እናንት ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ታምራትን፣ ድንቅ ነገሮችንና ምልክቶችን በእርሱ በኩል በማድረግ ለናዝሬቱ ኢየሱስ መስክሮለታል።
23 እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ፤ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።
24 እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና።
25 ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ ይላል፤“ ‘ጌታን ሁል ጊዜ በፊቴ አየዋለሁ፤እርሱ በቀኜ ነውና፣ከቶ አልታወክም።