ሐዋርያት ሥራ 8:31-37 NASV

31 ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።

32 ጃንደረባው ያነብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤“እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤የበግ ጠቦት በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፣እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

33 ራሱን በማዋረዱም ፍትሕን ተነፈገ፤ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና፣ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?”

34 ጃንደረባውም መልሶ ፊልጶስን፣ “ነቢዩ ይህን የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው፣ ወይስ ስለ ሌላ ሰው? እባክህ ንገረኝ” አለው።

35 ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚሁም መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት።

36 በመጓዝ ላይ ሳሉም ውሃ ካለበት ስፍራ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፣ “እነሆ፤ ውሃ እዚህ አለ፤ ታዲያ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው።

37 ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” ሲል መለሰለት፤